Thursday, August 18, 2011

ሙዚቃ

ሙዚቃ በሚያስተምረው ስንማር በሚያስተላልፈው መልእክት አብረን ስንተላለፍ
ዝንት
አለም አለፈ ። ማለት አንዱ የጥበብ ዘርፍ አልያም ክፍል ነው ።
ክብር ለጥበብ ፤ ለታላቋ የውስጣችን መገለጫ ለሆነችው የቅዱስ
ያሬድ እናት ፤ ክብር ለአንቺ አለምን በ አንድ ስምሽ ለምታግበቢ ።
በጭንቀት የታውከን አይምሮን በፍቅር ለምትፈውሺ....
ሙዚቃ የስንታችን
የፍቅር ስሜት ባንቺ ተገለጠ ። ስንቶቻችን ባንቺ
ውስጥ አልፈን በልባችን
ያመቅነውን
ሀዘንና ጭንቀት ተነፈስንበት ። በሚያሳዝነው ስናዝን በሚያስለቅሰውስናለቅስ አዲስ አለም ፡
- በሙዚቃ በዜማሽ በግጥምሽ በቃናሽ አለምን
አሳየሽን ። አሁንም ከብር ላንቺ ይሁን ። የነሞዛርት የቬትሆቨን ክብርት
እናት አለምን ያስደመምሽ ያስደነቅሽ ። ልባቸውን በሀሴት የሞላሽ ፍቅርን ለ አለም ያበሰርሽ ። የምታሳዘኚ የምታስደስቺ የምታስለቅሺ የምታስታርቂ የምታፋቅሪ..ሁሉን የማድረግ ጥበብ የሚገለጥብሽ የሚከወንበሽ ። የሁላችን የልብ
እናት ሙዚቃ
ከዝንት ዝንት ክፍለ ዘመን ስትሸጋገሪ እዚህ የደረሽ እድሜ በፍቅር የጠገብሽ የፍቅር
እናት አሁንም ደግሞ ደጋግሞ እድሜውን ያድልሽ ዘንድ ምኞቴ ነው ። ኑሪ
! ክበሪ !!
አሜን                                                                                                     ዳግም -ፍቅሩ
                                                                                                                   08/18/2011